Go back

Celebrating World Animal Day in Ethiopia

World Animal Day is celebrated every year in Ethiopia. The main event is celebrated by the Ministry of Livestock and Fisheries in Ethiopia, SPANA Ethiopia, Brooke Ethiopia, the DS Ethiopia, EVA and previously SAW.

WAD 2015 (2007 E.C.) in Shashemene town

ዓለምአቀፍ የእንስሳት ቀን

 ዓለምአቀፍ የእንስሳት ቀን በየዓመቱ እ.አ.አ. ኦክቶበር 4 ወይም በመስከረም 24 ወይም 25 ላይ እ.አ.አ ከ1931 ዓ.ም. ጀምሮ እንስሳትን በመዘከር እየተከበረ ይገኛል፡፡  ለዚህ ልዩ ቀን መመረጥ ምክንያት የሆነው አሲሲ ዘፍራንሲስ የተባለ በኢጣሊያ ይኖር የነበረ አንድ ቅዱስ ሰው ነው፡፡ ይህ ታላቅ ሰው ለእንስሳት እንዲሁም ለአከባቢ ጥበቃና ደህንነት ወደር የሌለው ፍቅር እንደነበረው ይነገራል፡፡ በዚህ ቅዱስ ሰው ክብርና ሞገስ አነሳሽነት በዚህ ዓለም የሚገኙ አያሌ ቤተክርስቲያናት ለመስከረም 24 ቅርብ የሆነ እሁድን በመምረጥ ለእንስሳት በተለይ የሚጸልዩበት ቀን በማድረግ ይዘክሩት ነበር፡፡ በመቀጠልም በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይወሰን እንስሳትን በሚያፈቅሩ ብዙ የሌሎች ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድም መከበር ከጀመረ ቀይቷል፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ በመስከረም 24 ወይም 25 እየተከበረ ይገኛል፡፡ በአንዳንድ ቦታም ከመስከረም 24-30 ለአንድ ሣምንት ያህል በተለያዩ ዝግጅቶችና መርሃግብሮች ይከበራል፡፡ ስለሆነም የዓለም የእንስሳት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ሲሆን በዜግነት፣ በኃይማኖት፣ በፖለቲካዊና ስለልቦናዊ አመለካከቶች ሳይገደብ ስለእንስሳት በሚደረጉ የተለያዩ በጎ ተግባራት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

 

የዝክረ ሣምንቱ ዓላማና ተልዕኮ፡-

*  የእንስሳትን ህይወት በሁሉም ገጽ ማክበር፣

*  የሰው ዝያ ከእንስሳት ወገን ያለውን ዝምድና ማክበር፣

*  እንስሳት ለሰው ልጅ ለሚሰጡት ዘርፈብዙ ጥቅሞች ዋጋ መስጠት፤ ማለትም በጓደኝነት የሚያገለግሉ የቤት እንስሳት፣ ኑሯችንን የተሳካ እንዲሆን የሚደግፉንና የሚረዱን እንስሳት አውቀን በክብር መቀበልና ተገቢውን ምስጋና መግለጽ ናቸው፡፡

ስለዚህ በዚህ ታሪካዊና ዓለምአቀፋዊ የእንስሳት ቀን ለእንስሳት ያለንን ፍቅርና ምስጋና እንዲሁም መቆርቆር በአንድነት እንድንገልጽና ስለእንስሳት ያለንን እውቀትና ግንዛቤ የምናሳድግበትና የምናበለጽግበት መድረክ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ 

ስለዚህ በግል፣ በድርጅት ወይም በቡድን በመሆን ለእንስሳት አምስቱ ነጻነቶች (አምስቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች) መከበር በአንድ ድምጽ የምንናገርበት፣ አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ ድርጊቶችን የምናከናውንበት መሆን ይኖርበታል፡፡ 
አምስቱ የእንስሳት ነጻነቶች ምንድን ናቸው?

በኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የእንስሳት ቀን መከበር የጀመረው በቅርብ ጊዜ ነው፡፡ በዓሉ በተናጠል ቀደም ብሎ በአንዳንድ የእንስሳት ደህንነት ድርጅቶች ሲከበር ቢቆይም በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤና ዳይሬክቶሬት ስር በተቋቋመው የእንስሳት ደህንነት ጉዳይ አንቀሳቃሽ ቡድን (Animal Welfare Working Group) በጋራ መከበር የጀመረው ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ በመሆኑም በ2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በግብርና ሚኒስቴር ግቢ፣ በ2003 ዓ.ም. ኡዴ ደንካካ መንደር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ በ2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ በ2005 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ፣ በ2006 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር እንዲሁም በ2007 ዓ.ም. በመቀሌ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በድምቀት ተከብሯል፡፡

Back to the top
Website by AgencyForGood

Copyright 2025. All Rights Reserved